Sunday, March 1, 2009

ዋስትና ያስያዘውን ጋዜጠኛ

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ለዋስትና እንዲያስይዝ የተጠየቀውን ብር 3000 ባለመክፈሉ ቃሊቲ የወረደው ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን የተጠየቀው የገንዘብ መጠን ከሙያ አጋሮቹና ከጓደኞቹ ተሰባስቦ ቢከፈልለትም የቃሊቲ ወህኒ ቤት ኃላፊዎች ግን ጋዜጠኛውን ለመልቀቅ ፍቃደኛ አልሆኑም ሲሉ ቤተሰቦቹ ገለጹ፡፡
የጋዜጠኛው ወላጅ እናት እንደገለጹት ልጃቸው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት የሚያስይዘው ገንዘብ ስላልነበረው ለተጠየቀው ዋስትና የሚሆን ገንዘብ እስኪገኝ ድረስ እስር ቤት መግባቱን ገልጸው አሁን ግን የሙያ አጋሮቹ አዋጥተውና የተጠየቀውን ገንዘብ በሙሉ ባለፈው ሀሙስ ለፍርድ ቤቱ ገቢ አድርገው ፍርድ ቤቱም እንዲለቀቅ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ሲያበቃ ‹የሚፈርም የማረሚያ ቤት ኃላፊ የለም› በሚል ምክንያት ልጃቸው ከአስር ቀን በላይ እስር ቤት ውስጥ እየተንገላታ መሆኑን በምሬት ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጧት ቃሊቲ ድረስ ሄደው ጋዜጠኛውን ጠይቀው የተመለሱ ቤተሰቦቹ እንዳሉት ጋዜጠኛው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መታሰሩን እንደገለጸላቸው አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የጋዜጠኛውን አካል ነጻ ለማውጣት ክስ እንደሚመሰርቱ ቤተሰቦቹ ገልጸውልናል፡፡