Sunday, March 1, 2009

ዋስትና ያስያዘውን ጋዜጠኛ

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ለዋስትና እንዲያስይዝ የተጠየቀውን ብር 3000 ባለመክፈሉ ቃሊቲ የወረደው ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን የተጠየቀው የገንዘብ መጠን ከሙያ አጋሮቹና ከጓደኞቹ ተሰባስቦ ቢከፈልለትም የቃሊቲ ወህኒ ቤት ኃላፊዎች ግን ጋዜጠኛውን ለመልቀቅ ፍቃደኛ አልሆኑም ሲሉ ቤተሰቦቹ ገለጹ፡፡
የጋዜጠኛው ወላጅ እናት እንደገለጹት ልጃቸው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት የሚያስይዘው ገንዘብ ስላልነበረው ለተጠየቀው ዋስትና የሚሆን ገንዘብ እስኪገኝ ድረስ እስር ቤት መግባቱን ገልጸው አሁን ግን የሙያ አጋሮቹ አዋጥተውና የተጠየቀውን ገንዘብ በሙሉ ባለፈው ሀሙስ ለፍርድ ቤቱ ገቢ አድርገው ፍርድ ቤቱም እንዲለቀቅ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ሲያበቃ ‹የሚፈርም የማረሚያ ቤት ኃላፊ የለም› በሚል ምክንያት ልጃቸው ከአስር ቀን በላይ እስር ቤት ውስጥ እየተንገላታ መሆኑን በምሬት ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጧት ቃሊቲ ድረስ ሄደው ጋዜጠኛውን ጠይቀው የተመለሱ ቤተሰቦቹ እንዳሉት ጋዜጠኛው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መታሰሩን እንደገለጸላቸው አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የጋዜጠኛውን አካል ነጻ ለማውጣት ክስ እንደሚመሰርቱ ቤተሰቦቹ ገልጸውልናል፡፡

Thursday, February 19, 2009

ቴዲ አፍሮ ከአምስት ወር በኋላ ይፈታል

ዝነኛው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በመኪና ሰውን ገጭቶ በማምለጥ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት በከፍተኛ ፍርድ ቤት የስድስት አመት እስራት እንደተፈረደበት ይታወቃል፡፡

ሆኖም ድምጻዊው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው ይግባኝ መሰረት ውሳኔው ተሸሮ በሁለት አመት እስራት ብቻ እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡

አውራምባ ያነጋገራቸው የህግ ባለሙዎች እንዳሉት ‹ያቀረበው የይግባኝ ሰነድ የቀረበበትን ክስ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ የሚያደርግ ነው ሆኖም የስርአቱ አገዛዞች ድምጻዊውን ነጻ ማድረግ ስላልፈለጉና ወንጀለኛ ነው እንዲባል ስለሚፈልጉ ነጻ ከማለት ይልቅ ሁለት አመት ብለው ፈርደውበታል› ብለዋል፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የቃሊቲ ወህኒ ቤት ኃላፊዎች እንደገለጹልን በወህኒ ቤቱ አሰራር መሰረት አንድ ፍርደኛ ከተፈረበት ፍርድ 1/3ኛውን በአመክሮ ስለሚቀነስለት የሚታሰረው አንድ አመት ከአራት ወር ብቻ ይሆናል ብለዋል፡፡ በዚህም መሰረት እስካሁን ለአስራ አንድ ወራት ያህል በእስር ቤት የቆየው ቴዲ ከአምስት ወር በኋላ ነጻ ይወጣል ተብሎ ይገመታል፡፡

አመክሮ የሚከለከልበት የተለየ ምክንያት አለ ወይ ስንል ጥያቄ ያቀረብንላቸው የወህኒ ቤት ምንጮች እንደገለጹልን አንድ ታሳሪ የተለየ መጥፎ የዲስፕሊን ችግር ከሌለበት በስተቀር ወይም ለማምለጥ ሙከራ ካላደረገ በቀር የአመክሮ ተጠቃሚ ይሆናል ቴዲ ደግሞ በሁሉም ዘንድ እጅግ የሚወደድ ባህሪና ጨዋ ስነምግባር ያለው ሰው እንደመሆኑ ይህ አይነቱ ክልከላ እርሱን አይመለከትም ብለውናል፡፡

በይቅርታ የተፈታው ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ወደቃሊቲ እስር ቤት ተመለሰ

(ኢትዮጵያን ሪቪው) - ምርጫ 97ን ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ከቅንጅት አመራሮች ጋር ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ታስረው በምህረት ከተፈቱ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን ከተፈታ ከአንድ አመት ከስድስት ወር በኋላ ዛሬ ወደቃሊቲ ወረደ፡፡

ከቅንጅት አመራሮች ጋር ታስረው የነበሩት ጋዜጠኞች በርካታዎቹ አገዛዙ ባደረሰባቸው ወከባና እንግልት ምክንያት አገር ጥለው ሲሰደዱ ከአምስት የማይበልጡቱ ደግሞ በአገር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነኚህ አምስት ጋዜጠኞች የፕሬስ ድርጅት ለማቋቋም ለማስታወቂያ ሚኒስቴር ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት ‹‹ፍቃድ የምንሰጠው ይቅርታ ፈርመው ለወጡ ጋዜጠኞች ብቻ ነው፡፡ ሲሳይ ሰርካለም እና እስክንድር ግን ፍርድ ቤቱ በነጻ ስላሰናበታቸው አሁንም ህገመንግስቱን ከመናድ ወደኋላ አይሉም፡፡ ይቅርታ የፈረሙቱ ግን ይቅርታቸው እንዳይነሳ ሁሌ እየሰጉ ስለሚሰሩ ይቅርታ የፈረሙበትን ሰነድ ዋናውና ፎቶኮፒ ይዘው ከቀረቡ ለጊዜው እንፈቅዳለን›› በሚል ርካሽና ከፋፋይ ምክንያት ለጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳንና ዳዊት ከበደ ብቻ ተፈቅዶ እያንዳንዳቸው ‹‹ሐራምቤ›› እና ‹‹አውራምባ ታይምስ›› የተሰኙ ጋዜጦችን አቋቁመው በመስራት ላይ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

ሆኖም አገዛዙ በሁለቱም ላይ በርካታ የክስ ዶሴዎችን ሲከምርባቸው እንደቆየ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን ባለፈው መስከረም በአስደንጋጭ ሁኔታ የህትመት ዋጋ ሲጨምር ወሰንሰገድ ‹‹ሐራምቤ›› ጋዜጣን መዝጋት ግድ ሆነበት፡፡

የአገዛዙ ግፍና ጭካኔ ግን በዚህ የሚቆም አልሆነም በሚያዚያ 2000 ዓ.ም የተደረገው ምርጫ እንደ1997ቱ ምርጫ ብዙ ህዝብ አልተሳተፈበትም፡፡ በየቦታው የነበሩ የምርጫ ጣቢያዎች ባዶ እንደነበሩና አስመራጮቹም ባዶውን ኮሮጆ ታቅፈው ሲያዛጉ መዋላቸውን በመዘገቡ ክስ ቀርቦበት ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ብር3000(ሦስት ሺህ ብር) ዋስትና እንዲያስይዝ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ሆኖም ጋዜጠኛው ለዚሁ የሚከፍለው ገንዘብ ባለማግኘቱ ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ተወስዷል፡፡

ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ወደ ቃሊቲ ከማቅናቱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አስተያየቱን እንዲሰጥ የኢትዮጵያን ሪቪው ዘጋቢ በልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተገኝቶ ጥያቄ አቅርቦለት ነበር፡፡ ወሰንሰገድ በሰጠው ምላሽ ‹‹በአስደንጋጭ የህትመት ዋጋ ጭማሪ ምክንያት መስራት ባለመቻሌ ደስ ይበላቸው ብዬ ስራውን ተውኩት የነበረኝ አነስተኛ ገንዘብ ደግሞ ለቀረቡብኝ በርካታ ክሶች ዋስትና አስይዤ ጨረስኩት፡፡ አሁን ግን ምንም የምከፍለው ስለሌለኝ ያለኝ አማራጭ መታሰር ነው›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

የአውራምባ ታይምስ ዋና አዘጋጅ አቶ ዳዊት ከበደም በተመሳሳይ ክስ በነገው ዕለት ከፍተኛ ፍርድቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Wednesday, January 21, 2009

የአውራምባ ታይምስ አዘጋጅ በ3000 ብር ዋስ ተለቀቀ

በአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ የሚያዝያ፣ግንቦትና ሰኔ ወር እትሞች ላይ በተስተናገዱ ሦስት ርዕሰ አንቀጾች፣ አንድ መጣጥፍና አንድ ቃለምልልስ ምክንያት ዓቃቤ ህግ ‹ህዝብን ለሁከት በማነሳሳት ወንጀል› ክስ የተመሰረተበት የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣና መጽሄት ዋና አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ዛሬ ረቡዕ ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስረኛ ወንጀል ችሎት በብር 3000 ሺህ ዋስ ለየካቲት 13/2001 እንዲቀርብ ብይን ሰጠ፡፡
ለዋና አዘጋጁ መከሰስ ምክንያት ከሆኑት ዘገባዎች መካከል በጋዜጣው የግንቦት 26 ቀን 2000 ዓ.ም ዕትም የወጣውና ‹ስልጣኔን እለቃለሁ ሲባል ስለ ትውፊትም(legacy) ማሰብ ተገቢ ነው› የሚል ርዕሰ አንቀጽ ይገኝበታል፡፡ጠ/ሚ መለስ በሶስት አመት ውስጥ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ በተናገሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ የተጻፈው ይህ ርዕሰ አንቀጽ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣን ሲረከቡ የገቧቸውን ቃሎች አለማክበራቸውን ብዙ ማስረጃዎችን በማቅረብ ይተነትንናል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እንደሚበላ የገቡትን ቃል አሁን ካለው በሚሊዮን የሚቆጠር ረሀብተኛ ወገን ጋር በማነጻጸር እንዲሁም በአገሪቱ ያለውን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር እጦት ያትታል፡፡ በመጨረሻም ርዕሰ አንቀጹ ይህም ሆኖ ጠ/ሚኒስትሩ በቀሯቸው ሦስት አመታት ለመልካም ትውፊት(legacy) ሲሉ መልካም ነገሮችን እንዲሰሩ ይጠይቃል፡፡
ሁለተኛው የአቃቤ ህግ ማስረጃ በግንቦት 12/2000 የተስተናገደውና ‹በንቅናቄው ዙሪያ የምንለውን ለማለት ወደድን› በሚል ርዕሰ የቀረበ ርዕሰ አንቀጽ ሲሆን ይዘቱም አንዳንድ ወገኖች በሰላማዊ ትግል ተስፋ እንዲቆርጡ ያደረጓቸው ምክንያቶች ገለልተኛ መሆን የሚገባቸው ዴሞክራቲክ ተቋማት ገለልተኛ ሆነው የቤት ስራቸውን ባለመስራታቸው እንደሆነ በመዘርዘር አሁንም እነኚህን የቤት ስራዎች መንግስት ካልሰራ በአሁኑ ሰዓት በሰላማዊ ትግል አምነው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ወገኖችም ተስፋ ቆርጠው ተመሳሳይ አቋም ሊይዙ ስለሚችሉ ዛሬውኑ በአገሪቱ ዴሞክራታይዜሽን ሂደት ውስጥ በስፋት ሊያሳትፍ የሚችል አሰራር እንዲዘረጋ ርዕሰ አንቀጹ ይማጸናል፡፡ በርዕሰ አንቀጹ ማሳረጊያም ላይ የሚከተለው ሀረግ ይገኝበታል ‹በመጀመሪያ ደረጃ ጋዜጣችን በህግ የበላይነት ታምናለች፡፡ በአገሪቱ ያሉ መጥፎም ይሁኑ ጥሩ ህጎችን(ህግ እስከሆኑ ድረስ) እናከብራለን ስለንቅናቄው አንስተን የምንነጋገረው ዜጎች በአገር ውስጥም በውጪም የሚደረጉ አገራዊ እንቅስቃሴዎችን የማወቅ መብት ስላላቸው ነው› ይላል፡፡ ለአዘጋጁ መከሰስ ምክንያት ነው ተብሎ በአቃቤ ህግ የቀረበው የዶ/ር መረራ ቃለምልልስ ሲሆን ‹እኔ የምመርጠው ቢራ እየጠጡ መታገልን ነው› የሚል ርዕስ ባለው ቃለምልልስ ከቀረቡ በርካታ ጥያቄዎች አንዱ ምን አይነት የትግል ስልት ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ያሰፍናል የሚል ይገኝበታል፡፡ ዶክተሩም የሌሎች አገሮች ተሞክሮን በማንሳት በምርጫ መምጣትና በትጥቅ ትግል መምጣት ብቻውን ዴሞክራሲያዊ መሪም ሆነ አምባገነን መሪ ለመሆን ምክንያት እንደማይሆን ገልጸው በምርጫ መጥተው አምባገነን የሆኑ መሪዎች የመኖራቸውን ያህል የኒካራጓው ሳንዲኒስታን የመሳሰሉ በትጥቅ ትግል ስልጣን ከጨበጡ በኋላ በምርጫ ተሸንፈው ከስልጣን በመውረድ እንደገና በሌላ ዙር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስልጣን የያዙበት ሁኔታ እንዳለ በመግለጽ እርሳቸውም ሆኑ ፓርቲያቸው ግን በሰላማዊ ትግል እንደሚያምኑ የገለጹበት ቃለምልልስ ይገኝበታል፡፡
ዋና አዘጋጁ ከጋዜጣው ጋር በተያያዘ በሌላ ተመሳሳይ ክስ የፊታችን ሰኞ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ይታወቃል፡፡

Saturday, January 10, 2009

New law ratchets up repression in Ethiopia

By Human Rights Watch

NEW YORK - On January 6, 2009, Ethiopia's parliament enacted a new law on nongovernmental organizations (NGOs) that criminalizes most human rights work in the country, Human Rights Watch said today. Human Rights Watch said that the law is a direct rebuke to governments that assist Ethiopia and that had expressed concerns about the law's restrictions on freedom of association and expression.

The action comes just a week after the government reversed an earlier pardon and rearrested one of the country's leading opposition politicians on flimsy grounds and said she will serve out a life sentence, highlighting a growing trend of political repression.

"In the space of just eight days, the Ethiopian regime has outlawed independent human rights work and jailed one of the country's most prominent opposition leaders for life," said Georgette Gagnon, Africa director at Human Rights Watch. "The government is conducting an all-out assault on any kind of independent criticism."

The Ethiopian government claims that the new law, known as the Charities and Societies Proclamation (NGO law), is mainly intended to ensure greater openness and financial probity on the part of nongovernmental organizations. But instead it places such severe restrictions on all human rights and governance-related work as to make most such work impossible, violating fundamental rights to freedom of association and expression provided for in the Ethiopian constitution and international human rights law.

The law considers any civil society group that receives more than 10 percent of its funding from abroad - even from Ethiopian citizens living outside of the country - to be "foreign." These groups are forbidden from doing any work that touches on human rights, governance, or a host of other issues. Because Ethiopia is one of the world's poorest countries, with few opportunities for domestic fundraising, such constraints are even more damaging than they would be elsewhere. Under the law, groups based outside the country, such as Human Rights Watch and Amnesty International, are barred from doing human rights-related work in Ethiopia.

The law also creates a new government entity, the Charities and Societies Agency, with sweeping powers and an arsenal of onerous and byzantine requirements that will enable it to choke off independent civil society activity with red tape. The right to appeal is severely limited and is not extended to so-called "foreign" groups at all. Human Rights Watch has produced a detailed analysis of a recent draft of this law. The enacted law is not substantially different from that draft.

"The NGO law is repression, not regulation," said Gagnon. "If enforced, this law will make Ethiopia one of the most inhospitable places in the world for both Ethiopian and international human rights groups."

Human Rights Watch said the law is especially alarming because the government already permits very little independent civil society activity or peaceful dissent. The country's preeminent human rights group, the Ethiopian Human Rights Council (EHRCO), is almost alone in producing extensive reporting inside Ethiopia on human rights abuses. In response to its reporting of government repression following Ethiopia's 2005 national elections, many of its staff were forced to leave the country or spent time in prison. Under the new law, the group will be considered a foreign human rights group because it receives most of its funding from international donors such as the National Endowment for Democracy in Washington, DC. It will either have to abandon its work or do without the funding it needs to meet its costs and pay its staff.

Countries that provide assistance to Ethiopia, including funds that keep the government afloat, have generally turned a blind eye to government abuses. However, many expressed private criticism of the NGO law, viewing it as a major step toward institutionalizing repression and creating impediments to development, which many support through Ethiopian NGOs. Human Rights Watch urged donor states to press for significant amendments to the new law or for its repeal. In the short term, they should urge the Ethiopian government not to enforce its most damaging provisions.

"Countries supporting Ethiopia should insist that the NGO law be substantially amended or repealed," Gagnon said. "Anything less would be a green light for even more egregious acts of repression in the coming year."

The new law is part of a broader trend toward political repression. Even though the country's political opposition has fractured since the 2005 elections and poses little real threat to government control, the authorities have continued to subject opposition leaders and activists to harassment and abuse. Within the past two months, the government has detained without charge two prominent opposition leaders. Bekele Jirata, the secretary general of the Oromo Federalist Democratic Movement, was arrested in November and accused of plotting terrorist attacks. He has been in prison for more than a month even though the government has failed to produce any evidence against him or file formal charges. On December 28, Birtukan Midekssa, chairperson of the opposition Unity for Justice and Democracy party, was arrested in the street and imprisoned on old charges that Human Rights Watch believes are politically motivated.

Birtukan had been arrested in November 2005 along with dozens of other opposition leaders who encouraged public protests after losing the controversial 2005 elections. Government security forces put down those protests by force, killing hundreds of unarmed demonstrators. Birtukan was convicted of attempting to overthrow the constitutional order and sentenced to life in prison. She was pardoned after lengthy negotiations and after she spent 18 months in prison. The government claims that her pardon was conditional on an apology for her crimes. It says it ordered her re-arrest over reports that she had publicly denied having apologized for her actions or asking for a pardon, and that she will now be imprisoned for life.

Ethiopia's already-dire human rights record has worsened in recent years. Ethiopian military forces have committed war crimes and crimes against humanity in two conflicts in Ethiopia and in neighboring Somalia, with no meaningful effort to hold those responsible to account. Federal, regional and local officials have regularly harassed, arbitrarily detained, and subjected to torture critics of the government, and have denounced human rights groups that expose these problems. As a result, there is little independent criticism and political opposition in most of the country. In local elections in April 2008, the ruling party and its allies won more than 99 percent of more than 4 million elected positions, most in uncontested races.

የዲኤች ገዳ ባለቤት በድንገት አረፉ

የዲኤች ገዳ ባለቤት የሆኑት ታዋቂው ባለሀብት አቶ ዱጉማ ሁንዴ በዛሬው ዕለት ህይወታቸው አለፈ፡፡ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሟች ባለሀብቶች ቁጥር ሦስት ደርሷል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት የካንጋሮ ፎም ባለቤት ልጅ የሆኑት የአሴ ማርብልና የአሴ ሴራሚክ ባለቤት እንዲሁም የጌታነህ ትሬዲንግ ባለቤት በተለያየ ምክንያት ራሳቸውን ያጠፉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የዲኤች ገዳ ባለቤት የሆኑት አቶ ዱጉማ ሁንዴ ለህልፈተ ህይወት መዳረግ ብዙዎችን አስደንግጣDል፡፡
መንስኤውን ለማጣራት አውራምባ ታይምስ ጥያቄ ያቀረበችላቸው የሟች ቤተሰቦች ለአቶ ዱጉማ ሞት ምክንያቱ ትንታ እንደሆነ ቢገልጹም ለባለሀብቱ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ግን ከባንክ ብድር ጋር በተያያዘ ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳለው ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸዋል፡፡

ወ/ሪት ብርቱካን ከወህኒ እንዲለቀቁ

መድረክ ለዴሞክራሲያዊ ትብብር በኢትዮጵያ በሚል ጥላ ስር ተሰባስበው በአገር ውስጥ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ የሚገኙት የኢትየጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት (ኢዴኃህ)፣የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ኦፌዴን)፣ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉአላዊነት (ዐረና) እንዲሁም የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት(ሶዴኃቅ) በዛሬው ዕለት ለአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በላኩት መግለጫ ወ/ሪት ብርቱካንም ሆኑ ሌሎች የቀድሞ ቅንጅት አመራር አባላት ጥፋተኛ የተባሉበትም ሆነ ይቅርታ የተደረገላቸው ‹ህገመንግስታዊውን ስርዓት በኃይል የመለወጥ ሙከራ› በሚል ክስ መሆኑ እየታወቀ ወ/ሪት ብርቱካን በተጠቀሰው ወንጀል ዳግም ተሰማርተው እስካልተገኙ ድረስ በውጪ ሀገር በተደረገ ስብሰባ ላይ ስለ ይቅርታው አቀራረብ ከተናገሯቸው ዓረፍተ ነገሮች አንድ ሀረግ ብቻ በመምዘዝ ይቅርታ ‹አልጠየኩም› ብለዋል በሚል ይቅርታው ተነስቶ እንደገና ለእድሜ ልክ እስራት መዳረጋቸው አሳስቦናል ብለዋል፡፡
እርምጃው ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጠበበ የመጣውን የሀገሪቱን ፖለቲካዊ ምህዳር ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይከተው ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብናል ያለው የፓርቲዎቹ መግለጫ ወ/ሪት ብርቱካን በተያዙበት ሰዓት አብሮአቸው በነበሩ ዜጎች ላይ ተወሰደ የተባለው ህገ ወጥ የሀይል እርምጃና እንግልት እንዳሳሰበውና በተለይ ‹ማንነታቸውን ባላሳወቁና ህጋዊ መጥሪያ ባላሳዩ ኃይሎች ተገደው እየተንገላቱ መወሰዳቸው የህግ የበላይነትን የጣሰና በብዙ ወገኖች ዘንድም ስጋት የጫረ እርምጃ ነው› ሲል ገልጻDል፡፡
ስለሆነም ይላል ይ¤ው መግለጫ ‹መንግስት ሁኔታውን እንደገና መርምሮ እና አጢኖ የተሰረዘው የወ/ሪት ብርቱካን ይቅርታ ውድቅ ሆኖ ቀደም ሲል የተሰጣቸው ይቅርታ ጸንቶ ከወህኒ እንዲለቀቁ እንዲያደርግ አበክረን እንጠይቃለን› ብሏል፡፡

Thursday, January 8, 2009

በጋዜጠኞች ላይ ሞት የጠየቁ አቃቤ ህግ

ከሁለት አመት በፊት ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊውን ስርዓት በሀይል የማፍረስ ወንጀል በሚል በጋዜጠኞችና በቅንጅት አመራሮች ላይ ክስ የመሰረቱና በኋላም በእነኚህ ተከሳሾች ላይ ሞት የጠየቁት አቃቤ ህግ ነጻውን ፕሬስ በበላይነት የመቆጣጠር ስልጣን ተሰጣቸው፡፡
የኢትየጵያ ብሮድካስት ኤጄንሲ ስራ አስኪያጅ፣በፍትህ ሚኒስቴር ረዳት ጠ/አቃቤ ህግ እንዲሁም የሌሎች ተደራራቢ ሹመቶች ባለቤት የሆኑትና በተለይ አፋኙን የፕሬስ ህግ በማርቀቅ የሚታወቁት አቶ ሽመልስ ከማል አፋኙ ህግ በፓርላማ በጸደቀ ማግስት ማስታወቂያ ሚኒስቴር በአዋጅ መፍረሱ ቢነገርም አፋኙ ህግ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ በኋላ ቀደም ሲል የማስታወቂያ ሚኒስትር ኃላፊነት የነበረው ነጻውን ፕሬስ የመመዝገብና የመቆጣጠር ስልጣን ሰሞኑን በአቶ ሽመልስ ከማል ለሚመራው ብሮድካስቲንግ ኤጄንሲ መሰጠቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለአውራምባ ገለጹ፡፡
እነኚሁ ምንጮች እንደገለጹልን ከሆነ እስከ ዛሬ ድረስ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት በሚገኝበት የማስታወቂያ ሚኒስትር ህንጻ 7ኛ ፎቅ ላይ የነበረው የፕሬስ ፈቃድ መምሪያ ዛሬ ሐሙስ ከሰአት በኋላ ኡራኤል አካባቢ ወደሚገኘው የብሮድካስት ኤጄንሲ ጽ/ቤት የቢሮ እቃዎቹን እያዛወረ ነው ሲሉ ለአውራምባ ታይምስ ገልጸዋል፡፡

Monday, January 5, 2009

ወ/ሪት ብርቱካን ዛሬም ሆነ ነገ ሊቀመንበራችን ናቸው

ከወላጅ እናታቸው ውጪ ማንም አልጎበኛቸውም

ከታሰሩ አንድ ሳምንት ያለፋቸውን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳን ለመጠየቅ ወደቃሊቲ ያቀኑ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የትግል አጋሮቻቸው ለአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍል እንደገለጹት ሊቀመንበሯን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ ካመሩ ወገኖች ውስጥ ከወላጅ እናታቸው ውጪ ገብቶ እንዲጠይቅ ለማንም አለመፈቀዱን አብራርተዋል፡፡በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ አውራምባ ታይምስ ጥያቄ ያቀረበላቸው የማረሚያ ቤቱ አስተዳዳሪ አቶ አበበ ዘሚካኤል ምንም አይነት ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ በበኩሉ በትናንትናው ዕለት ባወጣው ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ ‹ለእውነተኛ የህግ የበላይነት መከበር በጽናት ቆመው ለእስር የበቁ ሊቀመንበራችንን ለማስፈታት በመላው አለም ያሉ ኢትዮጵያዊያን የተቃውሞ ድምጻቸውን ያሰሙ› ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

Saturday, January 3, 2009

ሶማሊያ ውስጥ የሃይል ክፍተት አይኖርም ተባለ

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ወታደሮቹን ከሶማሊያ አስወጥቶ ሲጨርስ የሃይል ክፍተት እንደማይኖር በዛሬው ዕለት ማስታወቁን የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። ዘገባው የመንግሥቱን መግለጫ ጠቅሶ እንዳመለከተው የሃይል ክፍተትን ለማስወገድና የቀድሞው ሕገ-ወጥ ሁኔታ ተመልሶ እንዳይሰፍን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑት ዕርምጃዎች ተወስደዋል። የመንግሥቱ መግለጫ በሶማሊያ የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ፣ የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት ጦርና በሶማሊያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል መሪዎች ሁኔታውን ለማጤንና የተግባር ዕቅድ ለማውጣት ቀደም ሲል አዲስ አባባ ላይ ተገናኝተው ነበር። በሌላ በኩል እሥላም ዓማጺያን የኢትዮጵያ ወታደሮች በመውጣት ላይ እንዳሉ የፖሊስ ጣቢያዎችን እየያዙ መሆናቸውን የዓይን ምስክሮች እየተናገሩ ነው። የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት ወታደሮች እስካሁን በኢትዮጵያ ጦር እየተደገፉም የአገሪቱን ሁኔታ መቆጣጠር ሲሳናቸው በአንጻሩ እሥላማዊው የዓመጽ ቡድን አል-ሻባብ ሰፊ የአገሪቱን አካባቢ እየያዘ መምጣቱ ይታወቃል።

- DW-RADIO

ስሪላንካ፤ መንግሥት የዓማጺያኑን ይዞታ ተቆጣጠረ

የስሪላንካ መንግሥት ጦር ሣምንታት ከፈጀ ከባድ ውጊያ በኋላ በደሴቲቱ ሰሜን የምትገኘዋን የታሚል ዓማጺያን መናኸሪያ ኪሊኖቺን መቆጣጠሩ ተነገረ። የአገሪቱ ፕሬዚደንት ማሂንዳ ራጃፓክሤ ይህችው ለአሥር ዓመታት ያህል በታሚል ኤላም ዓማጺያን ቁጥጥር ሥር የቆየችው ከተማ ከመንግሥቱ ጦር ዕጅ መግባቷን በቴሌቪዥን ለሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ፕሬዚደንቱ ድሉን ታሪካዊ ሲሉ ዓማጺያኑ ሽንፈታቸውን እንዲቀበሉም አሳስበዋል። የኪሊኖቺ በመንግሥቱ ወታደሮች መያዝ በአንድ ለዓማጺያኑ ቀረብ ባለ የኢንተርኔት ድህረ-ገጽም ተረጋግጧል። ይህ በዚህ እንዳለ በኪሊኖቺ ድል የተበረታቱት የመንግሥቱ ወታደሮች በአካባቢው የምትገኘውን የወደብ ከተማ ሙላኢቲቩን ለመያዝ እየገፉ መሆናቸው እየተነገረ ነው። የታሚል ኤላም ዓማጺያን በደሴቲቱ ሰሜን-ምሥራቅ የራሳቸውን ነጻ ግዛት ለማቆም ሲታገሉ 25 ዓመታት አሳልፈዋል። በዚሁ ውዝግብ ሕይወታቸውን ያጡት ሰዎች 70 ሺህ ገደማ ይጠጋሉ።

- DW-RADIO

ሚልስ የጋና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆኑ

ጋና ውስጥ የተቃዋሚው ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ሸንጎ ዕጩ ጆን-አታ-ሚልስ ባለፈው ሰንበት ተካሂዶ የነበረው ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆኑ። ሚልስ ትናንት ቴይን በተሰኘችው ክፍለ-ሐገር በተጠናቀቀው ድምጽ ቆጠራ ከተፎካካሪያቸው ከመንግሥቱ ፓርቲ ዕጩ ከናና-አኩፎ-አዶ ልቀው መገኘታቸውን ጊዜያዊ ውጤት አመልክክቶ ነበር። በዚሁ ውጤት መሠረት ሚልስ 19.566 ድምጽ ሲያገኙ አዶ ያሰባሰቡት ድጋፍ በ 2,035 የተወሰነ ነው። የቴይን ምርጫ ትናንት የተካሄደው በድምጽ መስጫ ቅጾች ክፍፍል ረገድ በተፈጠረ ችግር ባለፈው ሰንበት ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ነበር። የአስመራጩ ኮሚሢዮን ሊቀ-መንበር ክዋዶ-አፋሪ-ግያሪ አጠቃላዩን ይፋ ውጤት ያስታወቁት ዛሬ ከቀትር በኋላ ላይ ነው። መንግሥታዊው ፓርቲ ተቃዋሚው ወገን ደጋፊዎቹ በሚያመዝኑበት በቮልታ አካባቢ አጭበርብሯል ሲል የቴይንን ምርጫ ለማስቆምና አስመራጩ ኮሚሢዮንም ውጤት እንዳያቀርብ ለማሳገድ ባለፈው ሐሙስ ለፍርድቤት ማመልከቻ አቅርቦ ነበር። ይሁንና ጥረቱ ሳይሰምርለት ቀርቷል።