Saturday, January 3, 2009

ሶማሊያ ውስጥ የሃይል ክፍተት አይኖርም ተባለ

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ወታደሮቹን ከሶማሊያ አስወጥቶ ሲጨርስ የሃይል ክፍተት እንደማይኖር በዛሬው ዕለት ማስታወቁን የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። ዘገባው የመንግሥቱን መግለጫ ጠቅሶ እንዳመለከተው የሃይል ክፍተትን ለማስወገድና የቀድሞው ሕገ-ወጥ ሁኔታ ተመልሶ እንዳይሰፍን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑት ዕርምጃዎች ተወስደዋል። የመንግሥቱ መግለጫ በሶማሊያ የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ፣ የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት ጦርና በሶማሊያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል መሪዎች ሁኔታውን ለማጤንና የተግባር ዕቅድ ለማውጣት ቀደም ሲል አዲስ አባባ ላይ ተገናኝተው ነበር። በሌላ በኩል እሥላም ዓማጺያን የኢትዮጵያ ወታደሮች በመውጣት ላይ እንዳሉ የፖሊስ ጣቢያዎችን እየያዙ መሆናቸውን የዓይን ምስክሮች እየተናገሩ ነው። የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት ወታደሮች እስካሁን በኢትዮጵያ ጦር እየተደገፉም የአገሪቱን ሁኔታ መቆጣጠር ሲሳናቸው በአንጻሩ እሥላማዊው የዓመጽ ቡድን አል-ሻባብ ሰፊ የአገሪቱን አካባቢ እየያዘ መምጣቱ ይታወቃል።

- DW-RADIO